ስለ የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር  በኢትዮጵያዉያን ወላጆች የሚነሱ የተለመዱ ጥያቄዎች

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር  ድርጅት  ምድነዉ?

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት ከኢትዮጵያ በጉድፈቻነት የተሰጡ ልጆችን መረጃ እና ልጆቻቸዉን የሚፈልጉ ወላጆችን መረጃ የያዘ የኢንተርኔት የመረጃ ቋት በመጠቀም የተጠፋፉ ወገኖችን ለማገናኘት የሚሰራ ተቐም ነው፡፡ይህ ማለት በከተሞች የሚንጠቀመዉን  የማስታወቂያ ሰለዳ እንደማለት ነው፡፡ ይህ የመረጃ ቋት በአሜሪካና አውሮፓ ለረጅም አመታት ሰዎች በጉዲፈቻ የተሰጡ ልጆችንና ወላጆችን ለማገናኘት ሲጠቀሙበት  የነበረ ዘዴ ነው፡:

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት እንዴት ሊረዳኝ ይችላል? ልጄ የት እንዳለች/እንዳለ ያዉቃል?

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት ልጅዎት የት እንዳለ/እንደለች አያውቅም፡፡ ነገር ግን ስለ ልጅዎ መረጃ ከእርስዎ በማግኘት ወደ መረጃ ቋት ያስገባል፡፡ ይህንን መረጃ ልጆችን ከኢትዮጵያ በጉድፈቻ ለወሰዱ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ለሚኖሩ ወላጆች ያካፍላል/ይሰጣል፡፡ ይህንን መረጃ ያገኙ/ የተመለከቱ  ወላጆች ሲጠይቁን እነዚህን ወላጆች ከእርስዎ ጋር እናገናኛለን፡፡ ይህ ሂደት ታዲያ በቀስታ የሚሆን ነገር ነው፡፡ ምናልባት የጉዲፈቻ ወላጆች መረጃዉን ሳያዩ ቢቀሩ እንኳን ልጆች ባደጉ ግዜ ይህንን መረጃ ያገኙታል ብለን እናምናለን፡፡

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት አገልግሎት ለማግኘት ስንት መክፈል አለብኝ?

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት ይህንን አገልግሎት ለመስጠት ምንም አይነት ክፍያ አይቀበልም፡፡ ይህ በነፃ የሚያገኙት አገልግሎት ነው፡፡

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት በፈለገኝ ግዜ እንዴት ሊያገኘኝ ይችላል?

እርስዎ በሰጡት ስልክ፣ ኢ-መይል፣ፖስታ አድራሸ ወይም እርስዎን በሚያውቅ አገናኝ ሰው በኩል መገናኘት ይቻላል፡፡

ልጄ በጉዲፈቻ የተወሰደችበትን/የተወሰደበትን  ሀገር ወይም የጉዲፈቻ ሂደቱን ያስፈጸመዉን አጀንሲ ስም ባላቀዉስ?

ችግር የለም እንደዛም ቢሆን የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት የመረጃ ቋት መጠቀም ይቻላል፡፡ እርስዎ የሚያዉቁትን መረጃ ብቻ በመጠቀም መስራት ይቻላል፡፡ ልጅዎ የነበረበትን ህጸናት ማቆያ ወይም ጉዲፈቻዉን ያስፈጸመውን አጀንሲ ወይም የአጀንሲዉን ሰራተኛ ስም በማወቅ የሄደበትን ሀገር ማወቅ እንችላለን፡፡

ጉዲፈቻ ስምምነት በተደረገ ወቅት ስለ ልጄ የሰጠሁት መረጃ የተሳሳተ/ውሸት ቢሆንስ?

በተለያዩ ምክንያቶች በጉዲፈቻ ስምምነት ወቅት የተሰጡ መረጃዎች  የተሳሳቱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህንን እዉነታ በጉድፈቻ የተሳተፍ ብዙ ወገኖች ያዉቁታል፡፡ ይህም ቢሆን እንረዳዎታለን በፍጹም የተፈጸመውን ስህተት ለሚመለከተው አካል አናመለክትም፡፡ ከልጅዎ ጋር በተገናኙ ግዜ ለጉዲፈቻ ወላጆች ስለ ሁኔታው ሊያስረዱ ይችላሉ፡፡

ስለ ልጄ ያለኝን መረጃ የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት መረጃ ቋት ካስገባሁት በኃላ በምን ያህል ግዜ ውስጥ ስለ ልጄ መስማት እችላለሁ?

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት  በዚህ ወቅት ስለልጅዎ  አንድ ነገር ይሰማሉ ብሎ ማረጋገጫ መስጠት አይችልም፡፡ ምክንያቱም  በመረጃ ቋት የገባዉን መረጃ የጉዲፈቻ ወላጆች መቼ ሊያዩት እንደሚችሉ እርግጠኛ መሆን ስለማይቻል፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን አንድ ጠቃሚ ሰው ያየዋል ብለን እናምናለን፡፡ በግዜ ሂደት ሰዎች ስለድርጅቱ ይበልጥ እያወቁ ሲመጡ ብዙ ሰው መረጃ ቋቱን ይጎበኘዋል ብለን እናምናለን፡፡ የእኛ አይነት የመረጃ ቋት በአደጉ አገራት የተለመዱ በመሆናቸው እና በጉዲፈቻ የተሰጡ  ልጆች ስለ  ኢትዮጵያ ወላጆቻቸው ማወቅ የሚፈልጉ በመሆናቸው ምክንያት ልጆች ባደጉ ግዜ ዛሬ እርስዎ የሰጡንን ይህንን መረጃ ያገኙታል፡፡

በጉዲፈቻ የተሰጠ ልጄን ማግኘት እንዴት ይህን ያህል ከባድ ሊሆን ቻለ?

የጉዲፈቻ ሂደትን ለማፋጠን ሲባል በወቅቱ  የተሰጡ መረጃዎች በብዛት የተሳሳቱ መሆናቸው አንደኛው ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ  ቤተሰቦችም ሆነ የጉዲፋቻ ወላጆች ትክክለኛ መረጃ የላቸውም፡፡ ይህ የተሳሳተ መረጃ የፍለጋ ሂደትን ከባድ ያደርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት ልጄን ከአገኘው በኃላ ቀጣይ ሂደት ምንድነው?

 የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት ከጉዲፈቻ ወላጆች ጋር ወይም 18 ዓመት የሞላው  ልጅ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያደርጋል ፡፡ ከዚህ ግንኙነት በኃላ ውሳኔው የጉዲፈቻ ወላጆች ወይም የአደጉ ልጆች ይሆናል፡፡ ከግንኙነቱ በኃላ የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ነገሮችን ይወስናሉ፡፡

ከሚከተሉት አንዱ ሊሆን ይችላል፡-

 • የጉዲፈቻ ወላጆች ከኢትዮጵያ ወላጆች ጋር መገናኘትን እምቢ ልሉ ይችላሉ
 • የጉዲፈቻ ወላጆች ወይም የአደጉ ልጆች (18 ዓመት የሞላቸው)ከሆኑ የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅትን እንደአገናኝ በመጠቀም ከኢትዮጵያ ወላጆቻቸው ጋር ግንኙነት ልጀምሩ ይችላሉ
 • የጉዲፈቻ ወላጆች ወይም የአደጉ ልጆች (18 ዓመት የሞላቸው) ከሆኑ በቀጥታ በስልክ፤ በኢ-መይል፤ በስካይፕ፤ ወይም በፌስ ቡክ ግንኙነት ሊያደርጉ ይችላሉ
 • የጉዲፈቻ ወላጆች ወይም የአደጉ ልጆች( 18 ዓመት) የሞላቸው ከሆኑ ደብዳቤና ፎቶ በየአመቱ ለኢትዮጵያ ወላጆቻቸው  ሊልኩ ይችላሉ
 • የጉዲፈቻ ወላጆች ወይም የአደጉ ልጆች (18 ዓመት) የሞላቸው በአካል መጥተው ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያ  ወላጆቻቸውን ሊጎበኙ ይችላሉ

  ልጄ ከተገኘ በኃላ ከኔ ጋር እንዴት ግንኙነት  ሳፈጥር  ቀረ?

የአደገ ልጅዎ(18 ዓመት) የሞላው ከሆነ ምናልባት ሁኔታዎች እስክመቻቹለት ድረስ እየጠበቀ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም አስክያድጉ ድረስ ስነገራቸው የነበረው የኢትዮጵያ ወላጆቻቸው እንደማይወዷቸው ወይም እንደሞቱ ተደርጎ ሲነገራቸው ቆይቶ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ስለ የኢትዮጵያ  ወላጆቻቸው ሲሰሙ ተደነጋግሮባቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በትዕግስትና ግዜ በመስጠት ጠብቋቸው፡፡

ልጅዎ ከ18 ዓመት በታች የሆነ እንደሆነ/ች በጉዲፈቻ ወላጆች የህግ ኃላፍነት ስር ናቸው ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ግዜ የ ጉዲፈቻ ወላጆች ልጆቹ ከኢትዮጵያ ወላጆቻቸው ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ ላይፈልጉ ይችላሉ፡፡ እንድህ በሆነ ግዜ  ልጅዎ 18 ዓመት በሞላው ግዜ እንዲያየው መረጃውን እንደገና እናስገባለን ፡፡

የሚከተለው ሀሳብ ስለሁኔታው  ይበልጥ ያብራረል

የጉዲፈቻ ወላጆች በብዛት የሚያምኑት ጉዲፈቻው ዝግ እንደሆነ ነው፡፡  ዝግ የሆነ ጉዲፈቻ ማለት በዋና ወለጆችና በጉዲፈቻ ወላጆች መካከል ምንም ዐይነት ግንኙነት የማይደረግበት ማለት ነው፡፡ እንዲህ በሆነ ግዜ ከዋና ወላጆች አንድ ነገር መስማት ያልተጠበቀና የሚያስፈራ ይሆንባቸዋል፡፡

በባህል ረገድ ከአውሮፓ ይልቅ  የአሜረካ እና የአውስትራሊያ ወላጆች ከኢትዮጵያ ወላጆች ጋር ለመገናኘት ፍላጎት አላቸው፡፡

የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር  ድርጅት ስያገኛቸው የጉዲፈቻ ወላጆች ምን ዓይነት ሚላሽ አላቸው?

የሚከተሉት ከሚላሾቹ አንዳንዶቹ ናቸው፡-

 • እነዚህ ሰዎች የልጄ ትክክለኛ የኢትዮጵያ ወላጆች መሆቻቸውን በምን አውቃለሁ?

-አንዳንድ የጉዲፈቻ ወላጆች ባለሙያ የሆነ አፈላላጊ በመቅጠር የኢትዮጵያ ወላጆች ትክክለኛነትን ማረጋገጥ ይፈልጋሉ፤ የደም ምርመራ በማድረግ እዉነተኛነቱን ማወቅ  የሚፈልጉም አሉ፡፡

-አንዳንዶቹ የጉዲፈቻ ቤተሰቦች በኤጀንሲ በኩል ሪፖርት ልክያለሁ ይላሉ ነገር ግን ይህ ሪፖርት የኢትዮጵያ ወላጆች ጋር ላይደርስ እንደሚችል በኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት በኩል ይነገራቸዋል፡፡

 • ከኢትዮጵያ ወላጆች ጋር ግንኙነት መፍጠር ህገ-ወጥ እንደሆነ ተነግሮኛል፤

-አንዳንድ ጊዜ  የጉዲፈቻ ኤጀንሲዎች ለጉዲፈቻ ወላጆች ከኢትዮጵያ ወላጆች ጋር ግንኙነት መፍጠር ህገ-ወጥ እንደሆነ ይነግሯቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ሀሰት ነው፡፡ በጉዲፈቻ ወቅት ቪዛ በማግኘት ረገድ የሚፈጠር የተሳሳተ እምነት ነው፡፡

 • የኢትዮጵያ ወላጆች ልጆቻቸውን መልሰው መውሰድ ቢፈልጉስ?

ጉዲፈቻው በህግ ፊት ህጋዊ እስከሆነ ድረስ ለኢትዮጵያ ቤተሰቦች ልጆችን መልሰው መውስድ በፍጹም ከባድ መሆኑን በኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት በኩል ይነገራቸዋል፡፡

 • ጉዲፈቻው ህጋዊና ሰነ.ስርዓት ያለው ነበር?

-ብዙን ግዜ ሰዎች ልጆችን በጉዲፈቻ የሚወስዱት ለመርዳት በመፈለግ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ወላጅ አልባ እንደሆነ የተገረ ልጅ ወላጅ እንዳለው ሲያውቁ ቁጭትና ንደት ውስጥ ይገባሉ፤ በዚህ ግዜ እምነት መጣል ከባድ ይሆናል ፡፡ የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት እንነደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች አንዳንድ ግዜ ሊፈጠሩ እንደሚችሉ  በመንገር የጉዲፈቻ ወላጆች ሁኔታውን እንዲረዱ ጥረት ያደርጋል፡፡

 • የኢትዮጵያ ወላጆች ገንዘብ ቢጠይቁኝስ?

በጉዲፈቻ ሂደት የወጪ ሀገር ወላጆች ለኢትዮጵያዉያን ወላጆች ገንዘብ እንዳይሰጡ በጉድፈቻ ኤጀንሲ በኩል ጥብቅ ማስጠንቀቂያ  ተነግሯቸዋል፡፡ ይህንን ካደረጉ ጉዲፈቻው ህገ-ወጥና ስነ ስርዓት ይጎደለው ይሆናል በማለት ጭምር፡፡ ስለሆነም  ለኢትዮጵያውያን ወላጆች ገንዘብ መላክ እና መርዳት ህግን መጣስ እንደሆነ ይቆጥሩታል፡፡

 • የኢትዮጵያ ወላጆችን የመርዳት ግዴታ አለብኝ?

የጉዲፈቻ ወላጆች የኢትዮጵያ ቤተሰብን የመርዳት ግዴታ የለባቸውም፡፡

 • ልጄ የኢትዮጵያ ወላጆቹ ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ዝግጁነት የለውም፤

-የጉዲፈቻ ወላጆች ልጁ ከኢትዮጵያ ወላጆች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር የሚወስንበት ዕድሜ ላይ አልደረሰም ገና ልጅ ነው ብለው ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ እንድሁም የኢትዮጵያ ወላጆች እየፈለጉት እንደሆነ እንኳን ልጁ ከአደገ በኃላ ለመንገር ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

 • የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት እንዴት አገኘኝ? ለምን ነበር የፈለገኝ?

-የጉዲፈቻ ወላጆች ኢትዮጵያ በጣም ሩቅ ሀገር እንደሆነችና ማንም ሊያገኛቸው እንደማይችል ያስባሉ፤ ሲለሆነም ከኢትዮጵያ ቤተሰብ መልዕክት ሲደርሳቸው በጣም ይደመማሉ አንዳንዴም ይናደዳሉ፡፡

እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ጉዳዮች  የኢትዮጵያ (ማደጎ) ወይም ጉዲፈቻ ትስስር ድርጅት የመረጃ ቋትን በመጠቀም ረገድ ያሉ ሂደቶችን ለመረዳት ያግዛሉ ብለን ተስፋ እናደርጋል፡፡ የበለጠ መረጃ ከፈለጉ ወይም ጥያቄ ካለዎት ይደውሉልን አማርኛ ተናጋሪ አባላት ጋር ልናገናኘዎት እንችላለን፡፡

አማርኛ

አሁን ይፈልጉ

መረጃውን ያስገቡ መመሪያ / ጥያቄዎቹ እዚህ ይጀምራሉ